የሀገር ውስጥ ዜና

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ ይጀመራል

By Meseret Awoke

March 25, 2022

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ በሰጡት መግለጫ ፥ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ሲካሄድ የቆየው የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፡፡

16 ተቋማትን ያካተተ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን አንስተው ፥ በዚህም ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ያሉ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለስ ስራ ይጀመራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ከ102 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን በአጭር ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ግብ ተቀምጦ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!