አዲስ አበባ ፣የካቲት 18 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ለቤት እንስሳት ምግብ በሚያቀርበው መተግበሪያ ላይ ተጠቃሚወች ቅሬታ ማቅረባቸው ተነግሯል።
መተግበሪያው በዘመናዊ ስልኮች በሚደርሰው መልዕክት አማካኝነት ለቤት ለእንስሳቶች ምግብ ያቀርባል።
ይሁን እንጂ መተግበሪው ከሰሞኑ በገጠመው ችግር ምክንያት በአግባቡ ለእንስሳቱ ምግብ እያቀረበ አለመሆኑን የእንስሳቱ አሳዳሪዎች ተናግረዋል።
ተጠቃሚዎች የቤት እንስሳቶችን ለመመገብ የሚያስችለው ቴክኖሎጂ እፎይታ እንደሚሰጣቸው አስበው ቢሸምቱም፥ በቴክኖሎጂው ላይ በሚከሰት ብልሽት ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ምክንያትም እንስሳቶቻቸው ለረሃብ መጋለጣቸውን ነው የተናገሩት።
መተግበሪው በብሪታኒያ በአማዞን የግብይት መተግበሪያ ላይ በ222 ዩሮ እየተሸጠ መሆኑ ተመላክቷል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision