Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብሪታኒያ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ እንዲሳለጥ ግጭት ማቆሙን አደነቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን ግጭት ማቆሙን አስታውቋል፡፡

ይህንኑ የመንግሥት ውሳኔ ተከትሎ ብሪታኒያ የኢትዮጵያ መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ በደስታ እንደምትቀበልና መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ምላሹን ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ማስታወቋን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን እና ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲደርስ ያሳለፈውን ውሳኔ በደስታ እንደምትቀበል አሳውቃ÷ በትግራይ ክልል በኩልም ተመሳሳይ ውሳኔ እንዲያሳልፉም ነው ጥሪ ያቀረበችው።

ብሪታኒያ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ምላሹን ለማሳደግ የኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗንም አሳውቃለች፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ሲባል ግጭት ማቆሙን ዛሬ መግለፁ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version