Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለአፋር እና ሶማሌ ክልሎች የ60 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለአፋር እና ሶማሌ ክልሎች የ60 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
የገንዘብ ድጋፉን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ በሰመራ እና ጅግጅጋ ከተማ በመገኝት አስረክበዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በስነ ስርአቱ ላይ÷ ድጋፉ በወሳኝ ወቅት ላይ የተደረገ በመሆኑ ለሕዝብ ያላችሁን ክብር አይተንበታል ብለዋል። ኢንቨስትመንት ግሩፑ በመልሶ ማቋቋም ሥራም እንዲያግዝም ጥሪ አቅርበዋል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በበኩላቸው÷ ድርቅ በክልሉ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልፀው ሚድሮክ ይህንን ድጋፍ ማድረጉ ትልቅ እርምጃ እና የአጋርነት ማሳያ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግስት ድርቁ ያደረሰውን ጉዳት ለመቀልበስ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ኢንቨስትመንት ግሩፑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እርዳታ ከመስጠት በተጨማሪ በክልሎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንደሚሰማራ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ጀማል አሕመድ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version