አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከግጭት እና አለመራጋጋት ወጥታ ልማትና ዕድገቷ እንዲሳካ ጀርመን የበኩሏን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ኃላፊ ቮን ኢሰን ማርከስ ገለጹ፡፡
የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ መክረዋል፡፡
በምስራቅ አፍሪካ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኘው ልዑኩ ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብርና ልማት ድጋፍ በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!