Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኔቶ አባል ሀገራት መሪዎች በብራሰልስ ተሰብስበዋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ-ዩክሬኑ ግጭትን አስመልክቶ የአጋር አካላት ሚናን መገምገምን ዓላማ ያደረገው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሀገራት መሪዎች ልዩ ስብሰባ ዛሬ በቤልጂየም፣ ብራሰልስ እየተካሄደ ነው፡፡
የመሪዎች ጉባኤው ከመጀመሩ አስቀድሞ መሪዎቹ በኔቶ ዋና መስሪያ ቤት የተለያዩ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን እንዳደረጉና ጉባኤው ቀጣይነት እንዳለው ተመላክቷል፡፡
በስብሰባው ኔቶ በምሥራቅ አውሮፓ ላይ ያለው የረዥም ጊዜ አቋም ምንድን ነው እና ሁለተኛ ወሩን በያዘው በሩሲያ – ዩክሬን ቀውስ ኔቶ የነበረው ሚና ምን ነበር የሚሉት ጉዳዮች ይገመገማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኔቶ ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ከስብሰባው መጀመር አስቀድሞ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፥ ሩሲያ የኬሚካል ጦር መሣሪያን ከተጠቀመች በዩክሬን ሕዝብ ላይ ትልቅ ጥፋት እና አስከፊ መዘዞችን ያስከትላል ማለታቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version