አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ40 ሺህ በላይ ለሆኑ የመንግስት አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ስልጠናው ብልፅግና ፓርቲ በሚያስተዳድርበት ሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ 39 ጣቢያዎች እየተሰጠ መሆኑን፥ የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አወሉ አብዲ ተናግረዋል።
በአመራሩ መካከል የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት እንዲፈጠር ማስቻል የስልጠናው ዓላማ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ከዚህ ባለፈም ሀገሪቱ አሁን ላይ እየተመራች ያለበትን እሳቤ አመራሩ እንዲገነዘብ ማድረግም የስልጠናው አላማ መሆኑንም ገልጸዋል።
አያይዘውም ስልጠናው እንደየ አካባቢው ሁኔታ ከ10 እስከ 15 ቀናት ይቆያል ብለዋል።
ስልጠናው በዋናነት የመደመር እሳቤ እና የብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ አስተሳሰቦች ምንነትና ይዘት ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሏል።
በኃይለሚካኤል ዴቢሳ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision