አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ኮምቦልቻና ደብረ ታቦር ከተሞች በብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ ፡፡
በኮምቦልቻ ከተማ በተካሄደው መድረክ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ እንድሪስ አብዱ እና የአማራ ክልል ሥራ አመራርና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አረጋ ከበደ እንዲሁም የጉባኤው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ አረጋ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር÷ ብልጽግና ፓርቲ ለሀገር ዕድገት መሰናክል የሆኑ ጉዳዮችን ከሕዝብ ጋር በመምከር መፍትሄ የሚፈልግ ፓርቲ መሆኑን ገልጸው÷ ዜጎች በነፃነት በመምከር ለኢትዮጵያ ዕድገት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በተመሳሳይ በደብረ ታቦር ከተማ በተካሄደው መድረክ የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ይርዳው÷ ለዘመናት የቆዩ የፖለቲካ ስብራቶችን መጠገን፣ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር እና የኅብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ችግር መፍታት ብልጽግና ፓርቲ በጉባኤው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች እንደሆነ ማስገንዘባቸውን ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በኢሳያስ ገላው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!