Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሁሉንም የማሕበረሰብ ክፍል ቀርበን ልናዳምጠው ይገባል ያልነው ብዙ የሚነግረን ነገር እንዳለ ስለምናውቅ ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሁሉንም የማሕበረሰብ ክፍል ቀርበን ልናዳምጠው ይገባል ያልነው ብዙ የሚነግረን ነገር እንዳለ ስለምናውቅ ነው ” ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ሲካሄድ በነበረው የህዝብ የውይይት መድረክ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሰብሳቢዎች የተነሱ ሲሆን÷ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች የተሰጡትን አስተያቶች በሙሉ እንደ ግብዓት እንደሚወሰዱ አረጋግጠዋል፡፡

በ121 ወረዳዎችና በ11 ክፍለ ከተሞች በተካሄደው መድረክ ÷̋ሁላችንም የየድርሻችንን ወስደን ጥያቄዎችን በሚገባቸው ቅደም ተከተል እየፈታን የምንዘልቅ ይሆናል ብለዋል፡፡

ትርክቶች፣ ሰንደቅ ዓላማና መሠል አጀንዳዎች በአገር አቀፍ ምክክሩ ላይ አጀንዳ ተደርገው ተይዘዋል ያሉት ከንቲባዋ÷ በዚያም መፍትሔ ያገኛሉ ብለን እናምናለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በበኩላቸው÷ አመራሮችን ማጥራት፣ የተቋማትን አሰራር መፈተሽ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ሌብነትን መታገል ፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የተመለከቱ ጥያቄዎችና ሌሎችንም ከሕዝቡ ጋር ተቀራርበን እየመከርን በጋራ እያረምን የምንሄደው የቤት ስራችን ይሆናል ብለዋል፡፡

አግላይነትን በማስወገድ፣ ልዩነትን ማጥበብ እና ሕዝባዊ አንድነታችንን በማጠናከር በጊዜ ሂደት ሕዝባችንን በማሣተፍ ፈተናዎቻችንን በመሻገር ላጋጠሙን ችግሮችም መፍትሄ እየሰጠን የምንሄድ ይሆናል ነው ያሉት ፡፡

ከሕዝብ የሚሰበሰቡ ጥያቄዎችን ወደ ዕቅድ በመለወጥ በሂደት ለተነሱ ጉዳዮች ተመጣጣኝ ምላሽ እየሰጠን እንሄዳለን ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ÷ ለስኬታማነቱም ሕዝባችን በሁሉም ረገድ ሊያግዘን ይገባል ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version