Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ያገለገሉበትን በሴኔጋል የኢትዮጵያን ኤምባሲን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘወዴ ለአራት ዓመት ያገለገሉበትን በሴኔጋል የኢትዮጵያን ኤምባሲን ጎብኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በሴኔጋል ዳካር እየተካሄደ በሚገኘው 9ኛው “ዓለም አቀፍ የውሃ ፎረም” ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
ከፎረሙ ጎን ለጎንም ያገለገሉበትን በሴኔጋል የኢትዮጵያን ኤምባሲን ጎብኝተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከ1981 ዓ.ም – 1985 ዓ.ም ድረስ መቀመጫቸውን ሴኔጋል በማድረግ በማሊ፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ጊኒ ቢሳዎ፣ ጋምቢያ እና ጊኒ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ማገልገላቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version