Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፈተናዎች መብዛት ከብልጽግና ጉዟችን አያስቆመንም – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈተናዎች መብዛት ከብልጽግና ጉዟችን አያስቆመንም ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ፡፡
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የከተማ ዓቀፍ የሕዝብ ውይይት መድረክ ተካሄዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
በተለይ የመብራት አገልግሎት ችግር በቅርቡ እንደሚፈታ እና ህብረተሰቡ ከመንግሥት ጎን ከሆነና ከተባበረ የህዝቡ ጥያቄ የማይመለስበት ምክንያት አይኖርም ማለታቸውን ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ርዕሰ መስተዳድሩ አያይዘውም የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር በህገወጥ ነጋዴዎች ላይ መንግሥት ክትትል በማድረግ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ጠቅሰው፥ ህብረተሰቡም እንደነዚህ ዓይነት ነጋዴዎችን በመጠቆም ትብበር እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በአካባቢው ያሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት ህዝቡ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ መሥራት አለበት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የክልሉ መንግሥትም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ፀጥታን ለማስከበርና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version