አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ከአዋሽ ባንክ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል እንደገለጹት÷ ብሔራዊ መታወቂያው በሚሰጠው ልዩ ቁጥር አማካኝነት ግለሰቦችን ለመለየት የሚያስችል ሲሆን ፥ በዚህም በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚደረግን ማጭበርበር ይከላከላል ብለዋል።
ከመታወቂያ፣ ከመንጃ ፍቃድና ከባንክ እንዲሁም ከተለያዩ አገልግሎቶች ጋር በመተሳሰር ደንበኛው በቀላሉ ማንነቱ ተለይቶ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችልም ነው የተናገሩት፡፡
ብሔራዊ መታወቂያ ለአንድ ሀገር ወሳኝ ነው ያሉት የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፀሀይ ሽፈራው÷ በተለይ የፋይናንስ አካታችነትን ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
በባንኮች አካባቢ ብዙ የማጭበርበር ሁኔታዎች መኖራቸውን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው÷ ለችግሩ መንስዔ ደግሞ ብሔራዊ መታወቂያ ባለመኖሩ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይህ ችግር እንደሚቀረፍም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ማንኛውም ግለሰብ የብሔራዊ መታወቂያ ካለው በቀላሉ በኦንላይን ብቻ ብድር ማግኘት ያስችለዋል ብለዋል።
በዓለምሰገድ አሳዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!