Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ጥሩ ሰላም ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
 
አደጋው ዛሬ ጠዋት 2 ሰአት ላይ ላንድ ክሮዘር መኪና ከባህር ዳር ወደ ሞጣ እየተጓዘ ባለበት ወቅት የጉዞ አቅጣጫውን ስቶ በግምት ከ600 እስከ 800 ሜትር ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ በመግባቱ መሆኑን ከሞጣ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በተከሰተው አደጋም የሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ÷ ሹፌሩን ጨምሮ በአምስት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በሽጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version