Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብልፅግና ፓርቲ የድህረ ጉባኤ የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የድህረ ጉባኤ ውይይት ከነዋሪዎች ጋር በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በውይይቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል ዶክተር እዮብ ተካልኝ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በመድረኮቹ በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ሃሳቦች ለቀጣይ ሥራ ግብዓት ሆነው ያገለግላሉ ተብሏል።
በጅግጅጋ ከተማ በህብረተሰቡ ይነሱ የነበሩ እና በመንግስት ምላሽ እየተሰጣቸው የሚገኙ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች መቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የሶማሌ ክልል ህዝብ ሰላምና ደህንነትን ቀጥሎ በኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የገለጹ ሲሆን÷ በክልሉ እየተካሄደ ያለው የውይይት መድረክ የክልሉን ህብረተሰብ የልማት ጥያቄዎች እንደሚፈታ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version