Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ አቅጣጫዎችን መነሻ ያደረገ የሕዝብ ውይይት ተጀምሯል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ውሳኔዎች፣ አቅጣጫዎችና አቋሞችን መነሻ ያደረገ የሕዝብ ውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በመድረኩም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ ብልጽግና ፓርቲ መላው ኢትዮጵውያንን እኩል ያሳተፈ መሆኑን ጠቁመው፣ ፓርቲው ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ለመፈጸምም ከአመራሩ ባሻገር ሕዝቡ ከፍተኛ ድርሻ ይጠበቅበታል ብለዋል።
በውይይቱም የብልጽግና ፓርቲ 1ኛ ጉባዔ ውሳኔዎች፣ አቅጣጫዎችና አቋሞችን ያካተተ ሰነድ በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢስሃቅ አብዱልቃድር እየቀረበ ነው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version