Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጋምቤላ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ድህረ ጉባዔ የህዝብ ውይይት መድረክ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል በአኙዋክ ብሄረሰብ ዞን በአቦቦ ወረዳ ከተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የብልጽግና ፓርቲ ድህረ ጉባዔ የህዝብ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የጋምቤላ ክልል ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ፥ ብልፅግና በጉባዔው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎችና አቋሞች ህዝቡ እንዲገነዘባቸው እና ለተፈፃሚነታቸውም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አቅም ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡

ብልፅግና በጉባዔው ያስቀመጠውን ውሳኔ ለህብረተሰቡ በማሳወቅ እና ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እንዲያስችል የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነም አንስተዋል፡፡

ብልፅግና ህብረተሰቡን ከድህነት ለማውጣት እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አፈ ጉባኤዋ ፥ ህብረተሰቡ ተማምኖበት የመረጠው እስከሆነ ድረስ ተያይዞ ለማደግ ተሳትፎ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የአኙዋክ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኡቦንግ ኡጁሉ በበኩላቸው ፥ ፍትሀዊ አካታች የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብልጽግና ትልቅ ዕድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል ፡፡

በሀገር ጉዳይ ላይ እኩል ተሳታፊና የውሳኔ ሰጪ አካል መሆኑ የለውጡ ማሳያ ነውም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version