አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ አጋር የልማት ተቋማት በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ የስርዓት ጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ እና በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ∶∶
በውይይቱ መንግስት የስርዓት ጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ ለኢትዮጵያ ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ወደ ብልጽግና የሚያደርሰውን የአስር ዓመቱን የልማት ዕቅድ በማቀድ ወደ ትግበራ መገባቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡
የስርዓት ጾታ እኩልነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ጥረት ያደነቁት ደግሞ በኢትዮጵያ የስፔን አምባሳደር ማኑኤል ሳላዛር ናቸው፡፡
የፖሊሲ ጉዳዮች፣ ጥምረትና የትግበራ ስራ ትኩረት የሚፈልጉ ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተው የገለጹም ሲሆን÷ እንደ ከዚህ ቀደሙ የሴቶችንና የልጃገረዶችን ህይወት በሚቀይር መልኩ የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰሩና አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የተናገሩት∶∶
በኢትዮጵያ የስርዓት ጾታ እኩልነት ለማረጋገጥ ከመስራት ባሻገር በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች መርዳት ላይም ከዓለም አቀፍ አጋር የልማት ተቋማት ጋር እንደሚሰራ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይ ሊካሄድ በታሰበው ብሄራዊ ውይይት የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ዓለም አቀፍ አጋር የልማት ተቋማት እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል∶∶
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!