Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጣሊያን የባህር ትራንስፖርት ኩባንያ በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 13፣2014(ኤፍ ቢ ሲ)የጣሊያን የባህር ትራንስፖርት ኩባንያ ሪሞርቺያቶሪ ዩኒቲ በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

ሪሞርቺያቶሪ ዩኒቲ የተሰኘው የጣሊያን የባህር ትራንስፖርት ኩባንያ ቡድን በኢትዮጵያ የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት አድርጓል።

የሪሞርቺያቶሪ ዩኒቲ ቡድን ከትራንስፖርት ሚኒስትሯና ሎጀስቲክስ ዳግማዊት ሞገስ ጋር ኩባንያው በኢትዮጵያ በዘርፉ ለመስራት በሚያስችለው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።

በዚህ ወቅትም በትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ያሉ እድሎች መመልከቱን ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል።

Exit mobile version