አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የሚገኘውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱ ኔዘርላንድስ ስዌል እና አሶሼት ኢንክ ከተባለ የአሜሪካ ኩባንያ ጋር በዛሬው እለት ተፈርሟል።ኩባንያው በሶማሌ ክልል ኦጋዴን አካባቢ 3 ሺህ 500 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የተሰሩ የፍለጋ እና የጥናት ውጤቶችን መነሻ በማድረግ በአካባቢው ያለውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መጠን የማሳወቅና ኢኮኖሚያዊ ግምገማን የሚያሳይ ጥናት ያካሂዳል ተብሏል።