አዲስ አበባ፣መጋቢት 13፣2014(ኤፍ ቢ ሲ) ዘመናዊ ያለሆኑ ነገር ግን በጥንካሬያቸው የሚታወቁት ባለውስን አገልግሎት ሞባይል ስልኮች እንደ አዲስ ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆናቸው ተገለፀ፡፡
እነዚህ ባለውስን አገልግሎት ስልኮች( dumbphones) ከዘመናዊ ስልኮች ጋር ሲነፃፀሩ በጣም ውስን የሆነ ተግባር ያላቸው የስልክ ቀፎዎች ናቸው፡፡
ባለውስን አገልግሎት ስልኮች የስልክ ጥሪዎችን እና አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን ብቻ መቀበል እንዲሁም የሬዲዮ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ከኢንተርኔት ጋር ግን ፍፁም ግንኙነት የላቸውም ፡፡
የአስራ ሰባት ዓመቷ የለንደን ከተማ ነዋሪ ሮቢን ዌስት “ከእኩዮቼ የምለይበት አንድ ምክንያት በፍፁም ዙመናዊ የሚባሉ ስልኮችን አለመጠቀሜ ነው” ስትል ትናገራለች፡፡
“በየቀኑ ቲክቶክ እና ኢንስታግራም ላይ ጊዜያቸውን ከሚያሳልፉ ጓደኞቼ በመለየት በምትኩ አኔ ባለውስን አገልግሎት ስልክ (dumbphone) ብቻ ነው የምጠቀመው” ትላለች።
ዌስት ከሁለት አመት በፊት የቀድሞ ስማርት ስልኳን ላለመጠቀም የወሰነችው በወቅቱ የምትጠቀምበት ዘመናዊ ስልክ ከትናንሽ ስልኮች ጋር የነበረው የዋጋ ልዩነት ከፍተኛ በመሆኑ ነበር፡፡
አሁን ላይ የምትጠቀምበት ባለውስን አገልግሎት ስልክ ዋጋው 8 ፓውንድ ብቻ ሲሆን ምንም አይነት የኢንተርኔት ግንኙነት ስለሌለው ለኢንተርኔት አገልግሎት የምታወጣው ምንም አይነት ገንዘብ እንደሌለ ትናገራለች፡፡
“ዘመናዊ ስልክ በነበረኝ ጊዜ ብዙ የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ነበሩኝ፤ ከመተግበሪያዎቹ ጋር አብዛኛውን ጊዜዬን ስልኬ ላይ አሳልፍ ነበር፣ ዘመናዊ ስልክ መጠቀሜ ህይወቴ ላይ ተፅዕኖ ነበረው” ትላለች ታዳጊዋ ሮብሲ፡፡
አሁን ላይ ግን ባለውስን አግለግሎት ስልክ ተጠቃሚ በመሆኗ ማህበራዊ ሚዲያ ከሚያመጣባት ተፅዕኖ በመላቀቅ ደስተኛ መሆኗን ገልፃለች፡፡
የቢቢሲ ዘገባ እንደሚያመላክተውም እነዚህ ባለውስን አገልግሎት ስልኮች( dumbphones) በተለያዩ የሶፍተዌር ኩባንያዎች እንደ አዲስ ለገቢያ እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡
2019 ላይ 400 ሚሊየን የነበረው የሽያጭ ቁጥራቸው አሁን ላይ 1 ቢሊየን ዩኒት መድረሱ ነው ቢቢሲ በዘገባው ያመለከተው።
እነዚህ በአንድ ወቅት ተትተው የነበሩ ስልኮች ከፈረንጆቹ 2018 እስክ 2021 ባሉት ዓመታት ውስጥ ጎግላይ የሚፈልጋቸው ሰው ቁጥር 89 በመቶ ጨምሯል።
ባለፈው የፈረንጆቹ 2021 ላይ በተገኘ መረጃ በብሪታኒያ ውስጥ ስልክ ካላቸው 10 ሰዎች ውስጥ አንዱ እነዚህ ባለውስን አገልግሎት ባለቤት ነው።
የዛሬ 22 ዓመት ገደማ ገበያው ላይ የምትታወቀው ኖኪያ 3310 ሞዴልም አሁን ላይ በድጋሚ በኩባንያው ተመርታ ወደገበያ መግባት ጀምራለች።
በጥንካሬ እና በባትሪ እድሜ ርዝማኔ የሚደነቁት እነዚህ ስልኮች አማራጮችን ውስን አድርገው ሰዎች በበርካታ ምርጫዎች ምክንያት የሚፈጠርባቸውን ጭንቀት ማቅለላቸው ዋነኛ ለተፈላጊነታቸው መጨመር ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!