አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ በሁለተኛ ቀን ጉባኤው የተለያዩ አዋጆች እና ደንቦች ላይ ውይይት እያደረገ ነው፡፡
የጨፌው አባላት የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅት አስተዳደርን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ፣’የቡሳ ጎኖፋ’ ባህላዊ የመረዳዳት ባህልን የሚያጠናክር አዋጅ፣ የስርዓቱ ጋሻ አዋጅ እና የጨፌ አባላት መተዳደሪያ ደንብ ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ የሚያሳልፍ ይሆናል።
እስካሁን ባለውም የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ልማት ድርጅት አስተዳደርን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን÷ በሌሎች ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።
ጨፌው በዛሬው ውሎው የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በአፈወርቅ አለሙ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!