አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ ፖስት 128ኛ የምስረታን በማስመልከት ልዩ የቴምብር ሙዚየም ማእከል ስራ ጀምረ፡፡
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት ፥ የኢትዮ ፖስታ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ዘመናዊ እና የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ተቋማዊ ቁመና በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡
በ10 ዓመቱ የልማት እቅድ እና በሎጂስቲክስ ሪፎርም ካቀዳቸው ዋና ዋና ተግባራት ዉስጥ የመጨረሻ መዳረሻ የሎጂስቲክስ አገልግሎትን ለማሳካት ጉልህ ሚና እንደሚጫወትም ነው የገለጹት፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!