Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ም/ ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
 
ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የ2014 የሰባት ወራት አፈጸጸም ገምግሞ በቀሪ የበጀቱ ዓመት ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን በመለየት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
 
የመስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉን ምክር ቤት የሕዝብ ተወካዮች ብዛት ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅም መርምሮ ለክልል ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡
 
በ2014 በጀት ዓመት የክልል ቢሮዎችና ተቋማት በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ያደረገው ም/ቤቱ÷ በዚህም ከአሁን ቀድም ለዞኖች የታወጀው 7 ቢሊየን 285 ሚለየን 599 ሺህ 3 መቶ 786 ብር እንደተጠበቀ ሆኖ ለክልል ቢሮዎችና ተቋማት ለመደበኛና ካፒታል ወጪ የሚውል 1 ቢሊየን 345 ሚሊየን 712 ሺህ 633 ብር ሆኖ በክልል ም/ ቤት እንዲጸድቅ ውሳኔ አሳልፏል።
 
በሌላ በኩል የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ከካፋ ዞንና ከምዕራብ ኦሞ ዞን የቀረቡ 11 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በቡና ልማት፣በሰብል ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ የስራ ዘርፎች ለመሰማራት 313 ሚሊየን ብር ካፒታል መጠን በማስመዝገብ ፈቃድ የጠየቁ ኢንቨስተሮችን ጥያቄ መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።
 
ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚውል 17 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ከመጠባበቂያ በጀት ስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ ማሳለፉንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version