Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት መልሶ ለማስቀጠል ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን አጠናቆ ነባር ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ ያሉ ተማሪዎች በበኩላቸው፥ የመማር ማስተማር ሂደቱ መልሶ መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በዩኒቨርሲቲው ላይ ያደረሰው ጉዳት እንዳሳዘናቸው ጠቁመው፥ ለመልሶ ግንባታው የተሰጠውን ትኩረት አድንቀው እየተሠራ ያለው ሥራም እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው፥ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ያለው የተረጋጋ የጸጥታ ሁኔታና ዝግጅት እንዳስደሰታቸው ጠቁመው፥ዩኒቨርሲቲው ወደ ቀድሞ ገጽታው በመመለሱ ያለስጋት ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲልኩ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version