አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰርቢያ -ቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ይዛ በማጠናቀቋ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷”በሰርቢያ-ቤልግሬድ በተካሄደው 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃን ይዛ ስላጠናቀቀች የተሰማኝን ደስታ እገልፃለሁ! እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!” ብለዋል፡፡
ቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ዓይነቶች በሁለቱም ፆታ 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡
ይህ ውጤትም የኢትዮጵያ ከፍተኛው የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ሆኖ የተመዘገበ ነው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!