አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም ከኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱ የሐይማኖት ተቋማት በሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና እና የሰላም ተልዕኳቸውን እንዳይወጡ በሚያደርጓቸው ተግዳሮቶች ዙሪያ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡
ሚኒስትሩ የሐይማኖት ተቋማት ሰላምን በማስፈን ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ገልፀው ፥ ይህን የሰላም ስራ በተሳካ ሁኔታ እንዲወጡ መንግስት ከጎናቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቦርድ አመራሮች በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ የሚገኙ ችግሮች ሰፊ መሆናቸው ጠቅሰው፥ ለመፍትሔው በጋራ መስራት እና መረባረብ ይገባል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!