Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኦሮሚያና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎችን የሚያገናኘው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልልን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚያስተሳስረው የአጋሮ-ጌራ-ሜዳቦ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

100 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀሙ በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ በመስክ የስራ ቅኝት ተገምግሟል።

በእስካሁኑ የሥራ እንቅስቃሴም ፤ የዲዛይን ሥራ፣ የካምፕ ግንባታ፣ የአፈር ቁፋሮ ሥራዎች፣ የጠጠር ማምረት፣ ኮንክሪት ፓይፕ ሥራዎች እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የአምስት ድልድዮች የግንባታ ስራ በፕሮጀክቱ የተካተተ ሲሆን ÷ከዲዛይን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን አጠናቅቆ በቅርቡ ወደ ሙሉ ግንባታ ለመሸጋገር በትኩረት እየተሰራ ነው ተብሏል።

ፕሮጀከቱ የሚከናወነው የኢትዮጵያ መንግስት በመደበው 3 ቢሊየን 170 ሚሊየን 122 ሺህ ብርመሆኑ የተገለፀ ሲሆን ÷ ግንባታውን ደግሞ ራማ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል/ማ እያከናወነ ይገኛል ።

የቁጥጥር እና የማማከር ሥራውን ኢንጂነር ዘውዴ እስክንድር አማካሪ ድርጅት እያካሄደ ይገኛል፡፡

መንገዱ አካባቢው የቅይጥ ግብርና እና የእንስሳት እርባታ በሰፊው የሚከናወንባቸው በመሆኑ እነዚህን የግብርና ውጤቶች ወደ ማዕከላዊ ገበያ በጥራት እና በፍጥነት ለማድረስ ያስችላል መባሉን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version