የሀገር ውስጥ ዜና

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ሰራዎችን በጥልቀት በመገምገም ልንሰራ ይገባል- ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

By Meseret Awoke

March 21, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ስራዎችን በጥልቀት በመገምገም እና ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ልንሠራ ይገባል ሲሉ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ፡፡

ሚኒስቴሩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ሁለተኛውን ዙር የ100 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸሙን የገመገመ ሲሆን÷ በመድረኩ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት የሁለተኛው ዙር እቅድ አፈጻፀም ላይ የተሰሩ ሰራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ በዘርፉ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስን መሠረተ ልማት የማስፋፋት ፣ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽነትን የማሻሻል፣ የጭነት ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት የገቢ ዕቃዎችን የወደብ ላይ ቆይታ የመቀነስ፣ የሦስተኛ ወገን መድን ሽፋንን ማሳደግ ላይ የተሰሩ ስራዎች በመድረኩ ተገምግመዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ህግ የማስከበር እንዲሁም የመንግስት የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ማሳደግ፣ በአቪዬሽን ዘርፍ የተሻሻለና ተደራሽ የሆነ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የመሰጠት ሰራዎች በትኩረት የተሰሩ ሰራዎች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሯ በትኩረት ሊሠሩ በሚገባቸዉ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር የሰራ መመሪያ ማስቀመጣቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!