ስፓርት

በዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ 4ኛ የወርቅ ሜዳሊያዋን በሳሙኤል ተፈራ አግኝታለች

By Mekoya Hailemariam

March 20, 2022

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር በመጨረሻው ቀን ከምሽቱ 2፡35 ላይ በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ሩጫ ሳሙኤል ተፈራ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።

ቀደም ብሎ በተካሄደ የ800 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ሩጫ ፍረወይኒ ኃይሉ 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

በውድድሩ ኢትዮጵያ አጠቃላይ በ4 ወርቅ፣ በ3 ብር፣ በ2 ነሃስ፣ በድምሩ በ9 ሜዳሊያ ከምንጊዜውም የአለም የቤት ውስጥ ውድድር በላቀ ውጤት ውድድሩን ጨርሳለች፡፡