አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አትክልት ተራ አካባቢ ለሚገነባው የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡
በክፍለ ከተማው አትክልት ተራ አካባቢ ከህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ከልማት መስፋፋት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ማዕከል ለመገንባት ከንቲባዋ የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ የፕሮጀክቱን ግንባታ በይፋ አስጀምረዋል።
ሕዝቡ በሚኖርበት አካባቢ ሁሉ የእሳት አደጋ ስጋቶችን በመለየት ለመቀነስ የበኩሉን ጥረት ሊያደርግ እንደሚገባ ከንቲባ አዳነች የመሰረት ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚያስፈልጋቸውን አካባቢዎች በመለየትና በማቋቋም ለሕዝቡ አኗኗር መሻሻል ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በተያዘለት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ክትትል እንደሚደረግም ማሳወቃቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ፍስሃ ፕሮጀክቱ ባለ 6 ወለል ሕንጻ መሆነቡን ጠቁመው÷ ለግንባታው የተያዘለት ጊዜ አንድ ዓመት ተኩል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅም ክትትል ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!