አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ዘርፍ የ8 ወራት አፈጻጸም መልካም የሚባልና ከፍተኛ ተስፋ የሚታይበት መሆኑን የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷በዛሬው ዕለት ከሁሉም ክልል የማዕድን ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የዘርፉን የስምንት ወራት የሥራ አፈጸጸም መገምገማቸውን ጠቁመዋል፡፡
በዚህም የግንባታ ግብዓቶች በመጠንና በጥራት እንዲቀርቡ ማድረግ፣ የወጪ ንግድ ምርቶችን በጥራት እና ብዛት መጨመር ላይ የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም አጠቃላይ የማዕድን ሀብቱ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለበት መንገድ መገምገሙን አንስተዋል፡፡
የዘርፉ የስምንት ወራት አፈጻጸምም መልካም የሚባል እና ከፍተኛ ተስፋ የሚታይበት መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ቀጣዩ ጊዜም የማዕድን ምርትን በመጠንና ጥራት አሳድገን ለዓለም ገበያ የምናቀርብበትና ለአገሪቱ የውጪ ምንዛሪ ማገር የምንሆንበት እንዲሁም ከውጭ የምናስገባቸውን ምርቶች በሂደት እየተካን የምንሄድበት ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!