Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ በለምለም ሀይሉ የመጀመሪያዋን ወርቅ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ በለምለም ሀይሉ የመጀመሪያውን ወርቅ አግኝታለች።
ማምሻውን በተካሄደ የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ለምለም ሀይሉ 8:41.82 በሆነ ሰዓት በመግባት አንደኛ በመሆን ወርቅ አስገኝታለች።
በውድድሩ እጅጋየሁ ታየ ሶስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር በ1 ሺህ 500 እና በ3 ሺህ ሜትር በሁለቱም ፆታ እየተካፈለች ትገኛለች።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version