አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ለደሴ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ክፍል መሳሪያዎችና ማሽኖሽን ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡
የሰዎች ለሰዎች የዕርዳታ ድርጅት በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት የደሴ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 6 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የቀዶ ህክምና አገልግሎት መስጫ መሳሪያዎችን እና ማሽኖችን በትናንትናው ዕለት ድጋፍ አድርጓል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ÷ በጦርነቱ የተጎዱ የጤና ተቋማትን የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ሁሉም አካላት ርብርቡን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ለደሴ አጠቃላይ ሆስፒታል ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!