Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ የቋንቋ ፕሮፋይል መለያ መስፈርት ላይ የተዘጋጀ ሰነድ ተገመገመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የቋንቋ ሥነ-ቃልና ትርጉም ሥራ ልማት ዳይሬክቶሬት በቋንቋ ፕሮፋይል መለያ መስፈርት ላይ ያዘጋጀው የማስፈጸሚያ ስትራቴጂክ ሰነድ ተገመገመ፡፡
የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ እንደገለጹት÷ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋዎች ባለቤት በመሆኗ የቋንቋ ፕሮፍይል ሰነድ መዘጋጀቱ የቋንቋዎችን ሙሉ መረጃ በቀላሉ ለማግኘት የሚረዳ ጥናት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትኖግራፊና የስነ- ልሳን ማንነት መግለጫ ሰነድ ያቀረቡት ዶክተር ባይለየኝ ጣሰው÷ ጥናቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ብሔሮች፣ ብሐረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም ምን ያህል ቋንቋዎች እንዳሉ ለማወቅ ይረዳል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህልና ቋንቋዎች መካከል ያሉትን ዝምድናዎችና ልዩነቶችን ለመለየት፣ እንዲሁም በመጥፋት አደጋ ውስጥ የሚገኙትንም ወቅታዊ ሁኔታና ደረጃ መግለፅን አላማ ያደረገ መሆኑ ተብራርቷል፡፡
ጥናቱ ቋንቋዎችና ባህሎች በእኩልነት እንዲታወቁ፣ እንዲያድጉ፣ እንዲበለጽጉና ለልማት እንዲውሉ እንዲሁም በየባህላዊ አውዶቻቸው እንዲጠኑ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘና መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version