ቴክ

አላስፈላጊ ሶፍትዌሮችና መተግበሪያዎች የትኞቹ ናችዉ?

By Meseret Awoke

March 18, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)አላስፈላጊ ሶፍትዌር የሚባለው አንድ ተጠቃሚ መተግበሪያዎችን ከበይነ-መረብ ሲያፈላልግ እና ሲያወርድ በስልክ አልያም በኮምፒዉተር ላይ ብቅ በማለት ራሳቸዉን የሚያስተዋዉቁ አላስፈላጊ የሆኑ መተግበሪያዎች ናቸዉ።

እነዚህ አላስፈላጊ መተግበሪያዎች በአብዛኛዉ ጊዜ ከሚፈለጉት ሶፍትዌሮች ጋር ተጣብቀዉ የሚመጡ ይገኛሉ።

በዚህ ሳቢያም ተጠቃሚዉ ሳያዉቅ እነዚህን መተግበሪያዎች ያለፍላጎቱ ተጭነዉ እና መገልገያዉን ሞልተዉ ሊያገኛቸዉ ይችላል።

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት የማይፈለጉ ሶፍትዌሮች እና መተግበሪያዎች ብሎ ካስቀመጣቸዉ መካከል ከዚህ በታች የተቀመጡት ይገኙበታል፦

የማስታወቂያ ሶፍትዌር ፡- ማስታወቂያዎችን የሚያሳይ ወይም ስለሌሎች ሶፍትዌሮች አገልግሎት የዳሰሳ ጥናቶች ላይ እንዲሳተፉ የሚጠይቅ የሶፍትዌር ዓይነት ሲሆን ፥ ከእነዚህ ሶፍትዌሮች መካከል በማስታወቂያዎች አማካኝነት ወደ ድረ-ገጾች እንዲገቡ የሚገፋፉ ሶፍትዌሮችን በዉስጣቸዉ ይይዛሉ።

የቶረንት ሶፍትዌር ፡- እነዚህ መተግበሪያዎች የአቻ ለአቻ ፋይል ለመጋራት እና ዳዉንሎድ ለማድረግ ጥቅም ላይ የሚዉሉ የሶፍትዌር ዓይነቶች ናችዉ።

ክሪፕቶማይኒንግ ፡- ይህ ሶፍትዌር የኮምፒዉተርዎን አልያም የስልክዎን ሃብት በመጠቀም ምስጢራዊ ምንዛሬዎች ለማውጣት የሚጠቀም ሶፍትዌር ዓይነት ነዉ።

የማርኬቲንግ ሶፍትዌር ፡- በመተግበሪያዎች ላይ ተጠቃሚዎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የሚከታተሉ እና ያለ ፍላጎታቸው መልዕክቶቹን የሚያስተላልፉ ሶፍትዌሮች ናቸዉ።

ሆኖም አንዳንድ ሕጋዊ ሶፍትዌሮች በእነዚህ መመዘኛዎች ተዳብለዉ በአላስፈላጊ ሶፍትዌር ማገጃ ሊያዙ ይችላሉ፡፡

እንደአብነትም የክሪፕቶ ማይኒንግ መተግበሪያዎች እና የቶሬንት ሶፍትዌሮች በተለምዶ ሕጋዊ ዓላማዎች አሏቸው ፤ ሆኖም አሁን ላይ ሶፍትዌሩ ተገኝቶ ሊወገድ እንደሚችል ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!