አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የምርት ዘመን ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርብ 30 ሺህ ቶን ቡና መሰብሰቡን በጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ ገለጸ።
በመምሪያው የቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ቡድን መሪ አቶ ሲሳይ በላይነህ÷በዘንድሮው አመት የዞኑ የቡና ምርት አያያዝ ከፍተኛ በመሆኑ 38 ሺህ ቶን ለማዕከላዊ ገበያ ይቀርባል ተብሎ እንደሚገመት ነው የገለፁት፡፡