Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አስፈላጊውን መረጃ ብንይዝም “በሲስተም መቋረጥ“ ምክንያት ከወልቂጤ ኬላ ማለፍ አልቻልንም- ቡና ላኪዎችና አሽከርካሪዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህጋዊ ቡና ላኪዎች ሆነን የሚጠበቅብንን ሙሉ መረጃ ብንይዝም “በሲስተም መቋረጥ” ምክንያት ከሳምንት በላይ ከወልቂጤ ኬላ ማለፍ አልቻልንም ሲሉ ቡና ላኪዎች እና አሽከርካሪዎች ቅሬታ አሰሙ፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት ማብራሪያ÷ በቦታው ያሉትን የስራ ኃላፊዎች ብንጠይቅም አጥጋቢ ምላሽ ሊሰጡን አልቻሉም፤ ቦታውም ሞቃታማ በመሆኑ ቡናው የመበላሸት ዕድል ይኖረዋል፥ ይህም ለኪሳራ ሊዳርገን ይችላል የሚል ስጋት አለን ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የገበያ መረጃና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ኬሩ ኑሩ በበኩላቸው ÷ ባለፉት 3 ቀናት እንደ ሀገር በሲስተም ችግር ምክንያት ስራ ቢቆምም አሁን ችግሩ ተፈትቷ ነው የሚሉት፡፡
በሌላ በኩል በጉምሩክ ኮሚሽን የጽፈት ቤት ኃላፊው አቶ ሙሌ አብዲሳ÷ በውጭ ንግድ ግብይት ችግር እንዳይገጥም በማንዋል ስራው እንዲሰራ ይደርጋል እንጂ÷በሲስተም መቋረጥ የውጭ ንግድ ግብይት እንዲቆም አይደረግም ነው ያሉት፡፡
አሁን ላይ ያጋጠመው ችግር ተፈትቶ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡
ለሳምንት ያህል ሲስተም ተቆርጦ ነበር የሚባለው ከእውነት የራቀ መሆኑንም ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version