የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት 10ኛ አስቸኳይ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

By Meseret Awoke

March 17, 2022

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት 10ኛ አስቸኳይ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የሚመሩት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 10ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የተጀመረው ዛሬ ከሰዓት በኋላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የካቲት 19 ቀን 2014 ዓ.ም የተካሄደውን ቃለ-ጉባዔ መርምሮ በማፅደቅ የተጀመረው ይህ አስቸኳይ ስብሰባ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፍል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ ከሚመክርባቸው አጀንዳዎች መካከል የቀጣይ ወራት ትኩረት በሚሹ ጉዳች ላይ የስራ አቅጣጫን ማስቀመጥ፣ ወጫቸውን መሸፈን ላልቻሉ ወረዳዎች የበጀት ድጎማ ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ላይ መምከር የሚሉት ይገኙበታል።

ለልማት ተነሺ ባለ ይዞታዎች የባህር ዛፋ ተክል ካሳ ክፍያ ማሻሻያ ረቂቅ ላይም ምክር ቤቱ ይመክራል ተብሏል።

የርዕሳነ መምህራን፣ ምክትሎች እና ሱፐር ቫይዘሮች የምልመላ፣ የስራ ስምሪትና የደረጃ ዕድገታቸውን በሚመለከት የቀረበ ማሻሻያም የሚመከርበት አጀንዳ እንደሆነም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክር ቤቱ በተጠቀሱና በሌሎች አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍም ይጠበቃል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!