የሀገር ውስጥ ዜና

የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ አስታወቀ

By ዮሐንስ ደርበው

March 17, 2022

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷የወደሙ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት በሚደረገው ጥረትም ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የኤጀንሲው የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ዶክተር ካትሱኪ ሞሪሀራ በበኩላቸው÷በፈረንጆቹ ከ2006 እስከ 2020 ከ290 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ መደረጉን ገልጸው÷በዚህም ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶችን መገንባት መቻሉን አብራርተዋል፡፡

ዋና ተወካዩ በጦርነት የወደሙና የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ተቋማቸው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደረግ ጠቁመው÷ ለትምህርት ቤቶች ከሂሳብና ሳይንስ ትምህርት ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችንና ቁሳቁሶችን እንደሚያሟላ  ማረጋገጣቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡