Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ዶክተር ካትሱኪ ሞሪሀራ ጋር ተወያይተዋል።
አሸባሪው ህወሃት በአማራ እና አፋር ክልሎች ወረራ ፈፅሞ በነበረባቸው አካባቢዎች ላይ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ላይ ሰፊ ውድመትና ዘረፋ መፈፀሙ ይታወቃል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷የወደሙ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት በሚደረገው ጥረትም ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የኤጀንሲው የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ዶክተር ካትሱኪ ሞሪሀራ በበኩላቸው÷በፈረንጆቹ ከ2006 እስከ 2020 ከ290 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ መደረጉን ገልጸው÷በዚህም ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶችን መገንባት መቻሉን አብራርተዋል፡፡

ዋና ተወካዩ በጦርነት የወደሙና የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ተቋማቸው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደረግ ጠቁመው÷ ለትምህርት ቤቶች ከሂሳብና ሳይንስ ትምህርት ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችንና ቁሳቁሶችን እንደሚያሟላ  ማረጋገጣቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version