አዲስ አበባ፣የካቲት 17፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አውስትራላዊቷ ሴት በወጣትነት ዘመኗ የጣለችውን ቀለበት ከ46 ዓመታት በኋላ ማግኘቷ ግርምትን ፈጥሯል፡፡
ከ46 ዓመታት በፊት ከእጮኛዋ የተሰጣት ይህ ቀለበት በብረታ ብረት ፈለጊ ባለሞያ ነው የተገኘው ተብሏል፡፡
ግሌንዳ ኦብሪየን የተባለችው ግለሰብ በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ1971 ታዳጊ በነበረችበት ፊሊፕ ከተባለ ግለሰብ የተሰጣት የጓደኝነት ቀለበት ስጦታ መሆኑን ገልጻለች፡፡
ቀለበቷ በፈረንጆቹ 1974 በኩዊንስላንድ ውስጥ በሚገኘው የመኖሪያ አፓርታማያቸው ውጭ መኪናዋን በምታጥብበት ወቅት እንደጣለችው ትጠረጥራለች ፡፡
ቀለበቱን ያገኙት ጃሰን ኬፕ ነራግ የተባሉት ግለሰብ እንደገለጹት÷ ከሦስት ወር በፊት የብረታ ብረት የመፈለግ ልማዳቸውን በሚከውኑበት ወቅት በቀድሞው የመኖሪያ አፓርታማ ላይ ቀለበቱን ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡
የወርቅ ቀለበቱን ሲያገኙት የባልና ሚስቱ የመጀመሪያ ስሞች የተቀረጸበት መሆኑን ጠቅሰው÷ በ8 ኢንች ቆሻሻ ክምር የተቀበረ ነበርም ብለዋል፡፡
በመቀጠልም በጎልድ ኮስት ማህበረሰብ የፍስቡክ ገጽ ላይ ስለቀለበቱ መለጠፉንና የኦቤሪን ትኩረት ማግኘቱን አስታውሷል፡፡
ኦብሪንም የጠፋባትን ቀለበት ዝርዝር ሁኔታና ቦታ በመላክ ቀለበቱን ያገኘው ግለሰብ የእቃው ባለቤት መሆኗን እንዲተማመን ማድረጓንም አክሎ ገልጿል፡፡
ኦብሪን አሁን ቀለበቱን ለልጅዋ በቤተሰብ ወራሽነት ለመስጠት ማቀዷም ነው የተነገረው፡፡
ምንጭ፡-www.upi.com