Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የታንዛኒያ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ፣ የመከላከያና የደህንነት ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የታንዛኒያ ፓርላማ የውጭ ጉዳይ፣ የመከላከያና የደህንነት ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ የፓርላማ አባላቱ በኢትዮጵያና በታንዛኒያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በበኩላቸው ÷ሁለቱ ሀገራት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ፣ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸውና በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም መስፋፋት እንዳለበት መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ታንዛኒያ የናይል ተፋሰስ ትብብር ስምምነት ማዕቀፍን ካጸደቁ ሀገራት ውስጥ አንዷ መሆኗ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version