Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዳይሬክተር ኬት ሀንሰን የተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን፣ በውሃ ሃብት አስተዳደርና በታዳሽ ኢነርጂ ልማት ዙሪያ እየሠራ ያለውን ስራ አስመልክቶ ለልዑካኑ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2030 ሁሉንም ዜጎቿን የኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዳ እየሠራች እንደሆነ መግለፃቸውን ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ኬት ሀንሰን በበኩላቸው እየተሠራ ያለውን ሥራ አድንቀው፤ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ሁሉም ዜጎቿ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የያዘችው እቅድ እንዲሳካ በትብብር ለመሥራትና ለማገዝ ፈቃደኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version