Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ሶማሊያ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዲኤታ ዴንገ ቦሩ እና የሶማሊያ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ኻሊፍ አብዲ ዑመር በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
የኢንዱስትሪና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አስተያየት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር በሚያስችል ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያና የሶማሊያ መንግስታት በድንበር ተሻጋሪ ንግድ ስምምነት ላይ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ያሉ ህዝቦችን ተጠቃሚ ለማድረግ እና ድንበር ተሻጋሪ ሕገ ወጥ ንግድን መቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ኮሜሳ እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን ጨምሮ በቀጠናው ውህደት ላይ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነት አድርገዋል።

የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እና የንግድ ልውውጡን ለመጨመር ሁኔታዎችን የሚያመቻች የጋራ የንግድ ኮሚቴ ለማቋቋም እንዲሁም የንግድ መድረኮችን ለማዘጋጀት፣ የባለሙያዎች ልውውጥ እና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሮችን ለማመቻቸት ተስማምተዋል።

በሁለቱም ሀገራት ሰራተኞችን፣ አርሶ አደሮችን እና የንግድ ሰዎችን የበለጠ የበለፀገ ውጤት ለማምጣት ሁለቱም ያላቸውን ከፍተኛ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version