Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል የወደሙ የውኃ ተቋማትን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጅ ቢሮ በአሸባሪው ህወሓት የወደሙና የተዘረፉ የውኃ ተቋማትን መልሶ ለመገንባትና ለመጠገን መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል።
 
ቢሮው እስካሁን የተዘረፉ የውኃ ተቋማትን መልሶ በመገንባትና በመጠገን ከሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
 
መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች መካከል ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ ካቶሊክ በጎ አድራጎት አገልግሎትና ኬር ኢትዮጵያ በመልሶ ግንባታ ሥራው አስተዋጽኦ እያደረጉ ካሉ ድርጅቶች መካከል ይገኙበታል ተብሏል፡፡
 
ቢሮው ድርጅቶቹ ወደ ፊት በሚያከናውኗቸው ተግባራት፣ በበጀትና በሥራ ስምሪት ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
 
የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት መካሄዱን አሚኮ ዘግቧል።
 
ድርጅቶቹ የሚያከናውኗቸው ተግባራትም ሰሜን ወሎ፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ደቡብ ወሎና ደቡብ ጎንደር ዞን አካባቢዎችን እንደሚያጠቃልል ዶክተር ማማሩ ተናግረዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version