አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በትምህርት ቤቶች የሶስት ወራት የጽዳት ንቅናቄ አስጀመረ፡፡
ንቅናቄው “ትምህርት ቤቴን አጸዳለሁ፤ ጽዱ እና ውብ በሆነ ከተማ እኖራለሁ! ” በሚል መሪ ሃቃል ነው የሚካሄደው
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የከተማ አስተዳደሩ የጽዳት አስተዳደር ዳይሬክተር ዶክተር እሽቱ ለማ እና የትምህርት ቢሮ አካላት ተገኝተዋል።
ንቅናቄውን የከተማዋ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጋራ የሚያከናውኑት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የጽዳት ዘመቻው በ570 ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የተገለጸ ሲሆን÷ በትምህርት ቤቶች ባሉ ክበባት የተለያዩ የግንዛቤ ስራዎች ይስራሉም ተብሏል።
የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ እና መልሶ መጠቀም እንዲሁም የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ተማሪዎች እንዲሰሩ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግም ተመላክቷል፡፡
ከመኖርያ ቤት የሚወጣው ደረቅ ቆሻሻ 76 በመቶ እና ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዝ ሲሆን÷ ከሆስፒታል የሚወጣው ደግሞ 1 በመቶ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!