አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በፈረንጆች 2022 በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ብቻ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ምርት 7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለጸ፡፡
ቻይና የኮቪድ ወረርሽኝ ቀውስ እና ሌሎች ዓለማቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ተውሳኮችን ተቋቁማ እመርታ ያለው ፈጣን እና ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበች ሲሆን በፈረንጆች 2022 በመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ብቻ 7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ማሳየቷን የሀገሪቱ ብሔራዊ ስታስቲክስ ቢሮ ገልጿል፡፡
ቻይና ከጥር እስከ የካቲት ወር በኢንዱስትሪ ምርት በተጨማሪ በችርቻሮ ሽያጭ እና በሌሎች ኢንቨስትመንቶች ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቧ ነው የተገለጸው።
ቢሮው በሰጠው ማብራሪያ በሀገሪቱ ብሄራዊ ኢኮኖሚ አገግሟል፤ የምርት ፍላጎት በፍጥነት አድጓል፤ ጤናማ የሆነ የሥራ ስምሪት እና የገበያ መረጋጋት ታይቷል፤ በአጠቃላይ እድገቱ ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያደርጉ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ፡፡
በቻይና አዲስ ኃይል የሚጠቀሙ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች እና የኢንዱስትሪ ሮቦቶች ማምረት ላይም ከፍተኛ እድገት መመዝገቡ ተገልጿል፡፡
የቻይና የአሁኑ አመት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የችርቻሮ ሽያጭ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ6 ነጥብ 7 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ዘገባው አስታውሷል።
የሀገሪቱ የቋሚ ንብረት ኢንቨስትመንት ከጥር እስከ የካቲት ወር በየአመቱ 12 ነጥብ2 በመቶ እንደጨመረም ተመላክቷል፡፡
በቻይና በመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት 8 ነጥብ1 በመቶ፣ በማኑፋክቸሪንግ 20 ነጥብ 9 በመቶ እና በሪል ስቴት ልማት 3 ነጥብ 7 በመቶ እድገት የታየ ሲሆን ይህም በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ጠንካራ እና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማሳያ መሆኑን አናዶሉ ዘግቧል።
በአመለወርቅ ደምሰው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!