Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት 623 መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በሁለት ዙር በተሰጠው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከተመዘገበው ውጤት 623 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በመጀመሪያው ዙር ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 563 ሲሆን÷ በሁለተኛው ዙር የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደግሞ 623 መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

ከፍተኛ ውጤቱም በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ የተመዘገበ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ፈተናው በመጀመሪያው ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ 500 የተያዘ ሲሆን÷ በሁለተኛ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600 መያዙ ታውቋል።

አጠቃላይ ፈተናውን በሁለት ዙር 598 ሺህ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን÷ ከዚህም ውስጥ 287 ሺህ 223 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152 ሺህ 14 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ምደባ እንደሚያገኙም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በመንግስት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63 ሺህ 833 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135 ሺህ 209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር ይችላሉም ተብሏል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version