ቴክ

ጎግል አዲስ የህዋዌ ምርት ተጠቃሚዎች መተግበሪያዎቼን እንዳይጠቀሙ ሲል አስጠነቀቀ

By Meseret Demissu

February 25, 2020

አዲስ አበባ፣የካቲት 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ኩባንያ በቅርብ ጊዜያት ወደ ገበያ የቀረቡ የሁዋዌ ስልኮች መተግበሪያዎቼን እንዳይጠቀሙ ሲል አስጠነቀቀ።

ጎግል ተጠቃሚዎች  አዲሶቹ ህዋዌ ስልኮች ላይ ተጽኖ የሚፈጥር  የጎግል መተግበሪያዎችን ደህንነቱ ካልተረጋገጠ ምንጭ ከመጫን እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ፡፡

የቅርብ ጊዜ የሁዋዌ ምርቶች የጎግል ፕሌይ መተግበሪያዎችን እንዲሁም  እንደ ጂሜይል ፣ ዩቲውብ  ወይም ጉግል ካርታ አይነት መተግበሪያዎችን ማውረድ እንደማይችሉም ተገልጿል፡፡

ነገር ግን የአንድሮይድ  ስልክ ተጠቃሚዎች  ደህንነታቸው ካልተረጋገጡ ምንጮች መተግበሪያዎችን መጫን መቻላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ይህን ተከትሎ  ጎግል  ተጠቃሚዎች  ደህንነታቸው ካልተረጋገጡ ምንጮች የሚያወርዷቸው  መተግበሪያዎች ከፍተኛ  አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል፡፡

የገበያ ጥናት ባለሙያ የሆነው  ቤን ውድስለ መተግበሪያው ታማኝነት መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን ካልተቻለ  ሃላፊነትን መውሰድ አይገባምም ብሏል፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ