Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ እና በሀርሱማ እና አፍዴራ ለተጠለሉ 7 ሺህ 500 ዜጎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ እና በሀርሱማ እና አፍዴራ ለተጠለሉ 7 ሺህ 500 ዜጎች ድጋፍ አደረገ፡፡

የድጋፉ ተጠቃሚዎች ከአባላ፣ በርሃሌ፣ ማጋሌ እና ኢሪብቲ አካባቢዎች የተፈናቀሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለ7 ሺህ 500 ዜጎችም የዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በጋራ በመሆን፥ የተለያዩ ድጋፎች መደረጉን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version